Friends of Amhara

PinterestFacebookTwitterInstagramLinkedInLinkSpotify

ምን እናድርግ ?

ሁላችንንም ወደፊት የሚያመጣ እንቅስቃሴ እየገነባን መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። የአማራ መበታተን እና በሕብረት ባለመቆማችን ክፉኛ አዳክሞናል ፤ ለጠላቶቻችን አጋልጦናል። ስለዚህ ካለፈው ስህተታችን ተምረን በአንድነት መቆም አለብን። ትግላችን በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መታደግ ነው።


እንደ ህዝብ ተደራጅተን ሁላችንም ለወገኖቻችን ዲፕሎማት ልንሆን ይገባል። ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፤ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እንዲገነዘቡ ማድረግ የኛ ኃላፊነት ነው ። በራሳችን ትግል እና መስዋዕትነት ፤ ነፃነታችንን ማስመዝገብ እንደምንችል ምንም ጥርጥር ባይኖረንም ፤ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ድጋፍ እስካላገኘን ድረስ የምንከፍለው መስዋዕትነት ብዙ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ስለሆነም የህዝባችን ጥያቄ የፍትሃዊ ጥያቄ  መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል።

Creeping Genocide: in Ethiopia by Dawit W Giorgis: Borkena

Lemkin Institute for Genocide Prevention: Statement on Ongoing Ethnic Massacres of the Amhara People in the Oromia Region of Ethiopia

February 3,  202

Ethiopia: Tigrayan forces murder, rape and pillage in attacks on civilians in Amhara towns

more than 200 killed in Ethiopia ethnic attack.

A National Dialogue for Transition in Ethiopia, By Dawit Giorgis

Ethiopia: Survivors of TPLF attack in Amhara describe gang rape, looting and physical assaults

Jemal Countess on the Ground in Amhara Region, Ethiopia

መደራጀት እና መታገል

አላማችን  ለአማራ ህዝብ ነጻነት በሚደረገው  የህልውና ትግል ላይ  የራሳችንን አስተዋጹኦ ለማበርከት ነው የአማራ ህዝብ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ  ፤ የግፍ ማዕበል እና አይን ያወጣ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ነው ። ለህዝባችን የሚጮህለት ፤ ከራሳችን በስተቀር አንድም ሃይል የለም።  የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም  በአማራ ላይ የሚፈሰመውን ወንጀል ፤ ሰምተው እንዳልሰሙ ፤ አይተው  እንዳላዩ ዝም ማለትን ምርጫ አድርገውታል ። ባጭሩ ለአማራ ህዝብ ከራሱ በስተቀር  ሌላ ማንም  እንደማይጮህለት ተረጋግጧል ። ለዚህም ነው ህዝባችን በብሄር ከመደራጀት ውጪ አማራጭ የለውም የምንለው።

ግንኙነት መፍጠር

በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሱበት ያለውን የጭካኔ ድርጊቶች ለአለም ህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ፣  በውጪ የሚኖረውን የአማራ ተወላጆችን በማሰባሰብና አንድ በማድረግ  ህዝባችንን ከጽንፈኛች  አገዛዝ ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ፤ በነፃነትና በክብር በታሪካዊ  የትውልድ አገራቸው መኖር  እንዲችሉ መታገል ነው ።

በአንድነት መቆም!

አማራ  በጅምላ የሚሞተው  እና  የሚፈናቀለው   መንግስታዊ መዋቀር  ስላለውና   ሆነተብሎ  በዕቅድ ስለሚፈጸም ነው ። በመሆኑም፦ እኛ አማራዎች ከልዩ ልዩ የሴራ አጀዳ ወጥተን እንደ አንድ አማራ በጋራ መቆም የግድ ይለናል ። በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን  አረመኔያዊ ተግባር በማውገዝና በማጋለጥ በተግባር ከወገኖቻችን ጎን እንቁም ። 




TBF. A podcast on Anchor

To address, whenever possible, other issues affecting human life such as health care, economic development, human right, environment, socio-economic aspects and women's issues.



Genocide is emerging on Ethiopia’s western front — Metekel. READ MORE

Crisis In Ethiopia: What the Media Isn't Telling You About the War In Tigray : READ MORE

Welkait, Ethiopia: Geo Strategic importance and the Consequential Annexation by TPLF : READ MORE

በአምባገነን  መንግስት ስር  የሚሠቃዩ ግለሰቦች ፤ አብዛኛውን  ጊዜ ፤ የምግብ ዋስትና  እና  የንጹህ  የመጠጥ ውሃ እጥረት  ይከሰታል ።  የመሠረታዊ  ትምህርት  ተደራሽነት አለመኖር ፤ በከፍተኛ  ድህነት ውስጥ  መኖር ፤  ጦርነት እና የእርስ  በርስ ግጭትን  መጋፈጥ ፤  ስደተኛ  መሆን ፤  የመናገር ነፃነት  እና  የመምረጥ  መብቶች አለመኖር ፤ በእስራት  መሰቃየት ፤ ሞት እና የማያቋርጥ  ማስፈራሪያ   ይደርስባቸዋል።

ኑ! ወዳጅ እንሁን! ለሚሰደዱት ፤ ለሚገደሉት ፤ ከርስታቸው ለሚፈናቀሉት የአማራ ወገኞቻችን አብረን እንምከር!በአንድ አካባቢ ከሆንን ስለ አማራው ሰባዊ መብት ጥሰት ፤ ግድያ እና መፈናቀል በሚደረግ ክስተት (ዝግጅት) አብረን እንመካከራለን ፤ በቀላሉ ግንኙነት እንመሰርታለን! በሚኖሩበት አካባቢ በሚደረግ ውይይት ወይም ሰላማዊ ሰልፍ ላይ አብረን ተሳታፊ  እንሆናለን ። ከሌለ ደግሞ  የራሳችንን ዝግጀት እናደርጋለን ፡፡  ኑ! ጓደኛ እንሁን ፤  መተዋወቅ መልካም ነው! 

ለአማራ ሕዝብ እንቅስቃሴ አድማና ሰላማዊ ሰልፍ ይውጡ! ወደፊት በአገር አቀፍ  ደረጃ ተቃውሞ ሰልፎችን እናደርጋለን!

በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በተለያዩ  ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ተጠቅመን በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንዲያውቀው እናድርግ። አላማችንን  በመደገፍ አጋር ይሁኑ ። ላልሰሙት ፤ መረጃ በማድረስ የበኩሎዎትን ሃላፊነት ይወጡ ። በአማራ ወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ጣልቃ በመግባት፤ የአማራ ማህበረሰብ ቀድሞ እራሱን እንዲጠብቅና እንዲከላከል መረጃ በመስጠትና በማስተማር ወገናዊ ሚናችንን እንወጣ።

ፍትህ እና ነጻነት ለአማራ ሕዝብ!

አዎ!  በአማራ ህዝብ ላይ እየደርሰበት ያለውን  የዘር ማጥፋት  ወንጀል እቃወማለሁ ።  በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን 

 ኢሰባዊ ወንጀል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ  ለማሳወቅ  በሚደረጉ  የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴዎች ላይ  እሳተፋለሁ ።

Massacre of about 300 Amhara civilians in East Wellega, inquiry commission is needed : READ MORE

PinterestFacebookTwitterInstagramLinkedInLink