What our graphic design services can do for you
ሁላችንንም ወደፊት የሚያመጣ እንቅስቃሴ እየገነባን መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። የአማራ መበታተን እና በሕብረት ባለመቆማችን ክፉኛ አዳክሞናል ፤ ለጠላቶቻችን አጋልጦናል። ስለዚህ ካለፈው ስህተታችን ተምረን በአንድነት መቆም አለብን። ትግላችን በአማራ ላይ የሚፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል መታደግ ነው።
እንደ ህዝብ ተደራጅተን ሁላችንም ለወገኖቻችን ዲፕሎማት ልንሆን ይገባል። ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ፤ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ እንዲገነዘቡ ማድረግ የኛ ኃላፊነት ነው ። በራሳችን ትግል እና መስዋዕትነት ፤ ነፃነታችንን ማስመዝገብ እንደምንችል ምንም ጥርጥር ባይኖረንም ፤ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ድጋፍ እስካላገኘን ድረስ የምንከፍለው መስዋዕትነት ብዙ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ስለሆነም የህዝባችን ጥያቄ የፍትሃዊ ጥያቄ መሆኑን ልናሰምርበት ይገባል።
Creeping Genocide: in Ethiopia by Dawit W Giorgis: Borkena
Lemkin Institute for Genocide Prevention: Statement on Ongoing Ethnic Massacres of the Amhara People in the Oromia Region of Ethiopia
February 3, 202
Ethiopia: Tigrayan forces murder, rape and pillage in attacks on civilians in Amhara towns
more than 200 killed in Ethiopia ethnic attack.
መደራጀት እና መታገል
አላማችን ለአማራ ህዝብ ነጻነት በሚደረገው የህልውና ትግል ላይ የራሳችንን አስተዋጹኦ ለማበርከት ነው። የአማራ ህዝብ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ፤ የግፍ ማዕበል እና አይን ያወጣ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ነው ። ለህዝባችን የሚጮህለት ፤ ከራሳችን በስተቀር አንድም ሃይል የለም። የአለም አቀፉ ማህበረሰብ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም በአማራ ላይ የሚፈሰመውን ወንጀል ፤ ሰምተው እንዳልሰሙ ፤ አይተው እንዳላዩ ዝም ማለትን ምርጫ አድርገውታል ። ባጭሩ ለአማራ ህዝብ ከራሱ በስተቀር ሌላ ማንም እንደማይጮህለት ተረጋግጧል ። ለዚህም ነው ህዝባችን በብሄር ከመደራጀት ውጪ አማራጭ የለውም የምንለው።
በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሱበት ያለውን የጭካኔ ድርጊቶች ለአለም ህዝብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ፣ በውጪ የሚኖረውን የአማራ ተወላጆችን በማሰባሰብና አንድ በማድረግ ህዝባችንን ከጽንፈኛች አገዛዝ ራሳቸውን መከላከል እንዲችሉ፤ በነፃነትና በክብር በታሪካዊ የትውልድ አገራቸው መኖር እንዲችሉ መታገል ነው ።
አማራ በጅምላ የሚሞተው እና የሚፈናቀለው መንግስታዊ መዋቀር ስላለውና ሆነተብሎ በዕቅድ ስለሚፈጸም ነው ። በመሆኑም፦ እኛ አማራዎች ከልዩ ልዩ የሴራ አጀዳ ወጥተን እንደ አንድ አማራ በጋራ መቆም የግድ ይለናል ። በአማራ ሕዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን አረመኔያዊ ተግባር በማውገዝና በማጋለጥ በተግባር ከወገኖቻችን ጎን እንቁም ።
To address, whenever possible, other issues affecting human life such as health care, economic development, human right, environment, socio-economic aspects and women's issues.
በሰላማዊ ሰልፍም ሆነ በተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ተጠቅመን በአማራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍ የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ እንዲያውቀው እናድርግ። አላማችንን በመደገፍ አጋር ይሁኑ ። ላልሰሙት ፤ መረጃ በማድረስ የበኩሎዎትን ሃላፊነት ይወጡ ። በአማራ ወገኖቻችን ላይ ለሚደርሰው ጥቃት ጣልቃ በመግባት፤ የአማራ ማህበረሰብ ቀድሞ እራሱን እንዲጠብቅና እንዲከላከል መረጃ በመስጠትና በማስተማር ወገናዊ ሚናችንን እንወጣ።
አዎ! በአማራ ህዝብ ላይ እየደርሰበት ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እቃወማለሁ ። በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን
ኢሰባዊ ወንጀል ለአለም አቀፍ ማህበረሰብ ለማሳወቅ በሚደረጉ የሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴዎች ላይ እሳተፋለሁ ።